አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ኢንቨስት እንዲያደርጉ በመጋበዝ እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለፁ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ገቢ ረሱ ዞን ገለዓሉ ወረዳ በ500 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚገኘውን የጥጥ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ባለሃብቶችን ማበረታታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ለባለሃብቶች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ኢንቨስት እንዲያደርጉ በመጋበዝ እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡