Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በትኩረት ይሰራል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝቡን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የ2017 የስራ ዘመን አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም ጀምሯል።

በዚሁ ወቅት አቶ ኦርዲን በድሪ÷ የመድረኩ ዓላማ በአንደኛ ሩብ ዓመት ለማከናወን በዕቅድ የተያዙ የልማት ግቦችን በመገምገም ጥንካሬ እና ጉድለትን በመለየት ለቀጣይ ጊዜ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የነባር ፕሮጀከቶች አፈፃፀም ደረጃ እና በበጀት ዓመቱ የተያዙ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን ብሎም የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸው በመድረኩ እንደሚገመገም ጠቁመዋል፡፡

በአንደኛ ሩብ ዓመት ሳይከናወኑ የቀሩ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ያልገቡበትን ምክንያት በመገምገም በ2ኛው ሩብ ዓመት ወደ ስራ የሚገቡበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋልም ብለዋል።

በቀጣይም ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በማረም የሕዝቡን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

በመድረኩ የሩብ ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም በኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ በከተማ ዘርፍ፣ ሰላም እና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አንፃር የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

የመስተዳድር ምክር ቤቱ ግምገማ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version