የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የመሠረተ-ልማት አጋርነት እንደሚያስቀጥል ገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

November 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር በቀጣይ በዘላቂ የከተማ እና መሠረተ-ልማት አጋርነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ቀጣናዊ ዳይሬክተር ሜሪዬ ሳሊም ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ለከተማ እና የመሠረተ-ልማት ግንባታ አጋርነት ላይ መምከራቸውን ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በዘላቂ የከተማ እና መሠረተ-ልማት አጋርነታችንን አጠናክረን ለመቀጠል ተስማምተናል፤ ይህም ለከተማ ብልጽግና ግባችን መሠረት ነው ብለዋል፡፡