አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሁለተኛ ዙር በከተማዋ እየተሰሩ የሚገኙ ስምንት የኮሪደር ልማት ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ ገምግመዋል::
ከንቲባዋ የኮሪደር ልማት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ በሚገባቸው ስራዎች ዙሪያ መወያየታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
በውይይቱ ከንቲባ አዳነች፤ በዕቅዳችን መሰረት ቅድሚያ የሚተገበሩ ተግባራትን በመለየት በጥራትና በፍጥነት ከተማችንን ውብ፣ ፅዱ፣ ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በትኩረት መስራት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበናል ብለዋል።
እንዲሁም እንደከዚህ ቀደም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ስራዎቹ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።