አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ በሚገኘው የ2024 ዓለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ዋንጫ አህጉራዊ ሻምፒዮና ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
ፕሬዚዳንቱ በስፖርት አካዳሚው ሲደርሱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በመርሐ ግብሩ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴዔታዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የስፖርት ማህበራት ፕሬዚዳንቶች መገኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡