የሀገር ውስጥ ዜና

የአክሱም ሐውልትን የጥገና ሥራ ወደ ተግባር ለማስገባት ስምምነት ተፈረመ

By Melaku Gedif

November 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአክሱም ሐውልት እና የነገስታት መቃብር ሥፍራን የጥገና ሥራ ወደ ተግባር ለማስገባት የጥገና ጥናት የውል ስምምነትና የቦታ ርክክብ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የአክሱም ሐውልት ቁጥር ሶስት እና በስሩ የሚገኙ የነገስታት መቃብር ሥፍራዎች ለማጥናት የማስጀመሪያ የፕሮጀክት ቦታ ርክክብ ዛሬ በአክሱም ከተማ አከናውኗል፡፡

ባለስልጣኑ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር የአክሱም ሃውልት ቁጥር 3 እና የነገስታት መቃብር ሙዚዬም እንዲሁም ‘ብሪክ አርክ’ የጥገና ጥናት ሙሉ ለሙሉ የመከለስ ሥራ፣ የጥገና ሥራው ተጽዕኖ ግምገማ ሰነድ ዝግጅት እንዲሁም በተግባር ጥገና ሥራ ወቅት የማማከር እና ክትትል ተግባር ለማከናወን የሚያስችል የውል ስምምነት ነው ከኤምኤች ኢንጅነሪንግና ስቱድዮ ክሮቺ ጋር የተፈራረመው፡፡