አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አራተኛ ዙር ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ።
ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ የቤልጂየሙ ክለብ ብሩጅ ከእንግሊዙ አስቶንቪላ፤ እንዲሁም የዩክሬኑ ሻካታር ዶኔስክ ከስዊዘርላንዱ ያንግ ቦይስ ጋር ይጫወታሉ፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 5 ሠዓት ሳንሲሮ ጁሴፔ ሜዛ ላይ ኢንተር ሚላን ከአርሰናል የሚያደርጉት ግጥሚያ የምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ ነው፡፡
በአርሰናል በኩል አምበሉ ማርቲን ኤዲጋርድ ከሁለት ወራት የቁርጭምጭሚት ጉዳት በኋላ ቡድኑን ተቀላቅሏል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 5 ሠዓት ላይ ባየርንሙኒክ ከፖርቹጋሉ ቤኔፊካ፣ የሆላንዱ ፌይኑርድ ከኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ ፒኤስጂ ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ የሰርቢያው ሬድ ስታር ቤልግሬድ ከባርሴሎና፣ የቼክ ሪፐብሊኩ ስፓርታ ፕራግ ከፈረንሳዩ ብረስት እንዲሁም የጀርመኑ ስቱትጋርት ከጣሊያኑ አትላንታ ይፋለማሉ፡፡
ትናንት ምሽት በተደረጉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ማንቼስተር ሲቲ በስፖርቲንግ ሊዝብን 4 ለ 1 እንዲሁም ሪያል ማድሪድ በሜዳው በኤሲሚላን 3 ለ 1 ተሸንፈዋል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ሊቨርፑል ባየርሊቨርኩሰንን 4 ለ 0፣ ፒኤስቪ ዢሮናን 4 ለ 0፣ ሴልቲክ አር ቢ ሌይቢዢግን 3 ለ 1፣ ቦሩሺያ ዶርቱመንድ ስትሩም ግራዝን 1 ለ 0፣ ሞናኮ ቦሎኛን 1 ለ 0፣ ዳይናሞ ዛግሬብ ስሎቫን ብራቲስላቫን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸነፉ ሲሆን ሊል ከጁቬንቱስ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡