የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል አነስተኛ ገቢ ላላቸውን ወገኖች ቤት ለመገንባት የተያዘው እቅድ ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

By Mikias Ayele

November 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የተያዘው እቅድ ውጤታማ እየሆነ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳደሩ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ያለውን የከተማውን የኮሪደር ልማት ስራ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት፤ ለሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ትኩረት በመስጠት ለአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እየተከናወነ ነው።

በተጨማሪም የዜጎችን ኑሮ የማሻሻል እና የመልሶ ልማት ስራዎች እየተከወኑ ነው ብለዋል።

ባህር ዳር፣ ደሴ እና ጎንደር ከተሞች የኮሪደር ልማቱን እያፈጠኑ በተገቢው መንገድ እየሰሩ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፤ ኮምቦልቻም በኮሪደር ልማቱ ጥሩ ጅማሮ ላይ መሆኗን አንስተዋል።

በክልሉ ባለፉት አምስት ዓመታት አነስተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የተያዘው እቅድ ውጤታማ እየሆነም ተናግረዋል።

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር እስከ አሁን 42 የዝቅተኛ ነዋሪዎች ቤት ተገንብቶ መተላለፉ የተነሳ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ለአንዲት አቅመ ደካማ የተገነባ መኖሪያ ቤት ቁልፍ ርዕሰ መስተዳድሩ አስረክበዋል።

በስንታየሁ አራጌ