የሀገር ውስጥ ዜና

ፋኦ በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የመጣውን ተጨባጭ ለውጥ ለማስቀጠል ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

By amele Demisew

November 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የመጣውን ተጨባጭ ለውጥ ለማስቀጠል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከአለም የምግብና እርሻ ድርጅት የምጣኔ ሃብት ዋና ኃላፊ ማክሲሞ ቴሬሮ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በግብርናው ዘርፍ በቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ በሚያደርገው ጥረት የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት፤ በገንዘብ፣ በሙያ እና በአቅም ግንባታ ለሚያደርገው ድጋፍ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአለም ምግብና እርሻ ድርጅት የምጣኔ ሃብት ዋና ኃላፊ ማክሲሞ ቴሬሮ በበኩላቸው ÷በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ላለው ተጨባጭ ለውጥ እውቅና ሰጥተው ፤በቀጣይም ፋኦ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡