አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምን ለማጽናት እየተከናወነ ባለው ሂደት የመንግሥት ሠራተኛው የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡
የደብረብርሃን እና የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግሥት ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች ቡድን መሪዎች የተሳተፉበት መድረክ “ሠላም ለሁሉም ሁሉም ለሠላም”በሚል መሪ ሐሳብ ተካሂዷል፡፡
በመከላከያ ሰራዊት የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ በመድረኩ ላይ እንዳሉት÷ የመከላከያ ኃይሉ በከፈለው መስዋዕትነት በአካባቢው ሰላም እየመጣ ነው።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ በበከሉላቸው÷ ሰላምን ለማጽናት እየተከናወነ ባለው ሥራ የመንግሥት ሠራተኛው የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊ የመንግሥት ሠራተኞች በክልሉ ያጋጠመው የሰላም እጦት በውይይትና በሰላም እንዲፈታ ጠይቀው÷ በእነሱ በኩልም የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡
በግርማ ነሲቡ