Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሀሰተኛ ደረሰኝ፣ የብር ኖቶችና ሠነዶች ህትመት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ በሀሰተኛ ደረሰኝ፣ በሀሰተኛ የብር ኖቶች እና ሠነዶች ህትመት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

ተጠርጣሪዎቹ አቶ አንዋር አለማየሁ እና አቶ ኢማም ሰይድ ፍቃድ ሳያወጡ ማተሚያ በመክፈት የተለያዩ የብር ኖቶች፣ ሀሰተኛ ሰነዶች፣ ህገ-ወጥ የተለያዩ ተቋማት ማህተሞች እና ለዚሁ ህትመት ተግባር የሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮችና ፕሪንተሮች ጨምሮ ተይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ ክ/ከተማ ኦዳ ወረዳ ኢምሩ በተባለ ህንፃ ላይ በተከራዩት ሱቅ ውስጥ ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር ሲያከናውኑ እንደነበረ ተደርሶበት በተጠርጣሪዎቹ ላይም የምርመራ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል፡፡

በዚሁ ክ/ከተማ በተመሳሳይ ቦታና ህንፃ ሌላ ሱቅ ከፍቶ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያትም የነበረ ግለሰብም በዚሁ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተጠርጣሪው አቶ ዳንኤል ሸዋለማ የንግድ ፍቃድ የሌለው ማተሚያ ድርጅት በመጠቀም የተለያዩ ደረሰኞችን፣ ሠነዶችንና ማህተሞችን በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረጉ ተገልጿል፡፡

Exit mobile version