Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ጠቅላላ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ጠቅላላ ጉባዔ እና የተሞክሮ ልምድ ልውውጥ መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የከተማ ልማትና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን፣ ከ100 የሚበልጡ ከተሞች አስተዳደሮች ከንቲባዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የትብብር መድረኩ በከተሞች የሚከናወኑ መሰረተ ልማቶችን በማጠናከር ከተሜነትን ለማስፋፋትና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የሚያግዙ ጉዳዮች የሚዳሰሱበት መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም ከንቲባዎችና ሌሎች የአመራር አባላት ልምድ በመለዋወጥ በከተሞች የሚታዩ ችግሮችን ለማቃለል የሚያስችል አቅም የሚፈጥሩበት መሆኑ ተገልጿል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባዔው በኢትዮጵያ ከተሞች ማህበራዊና ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ ጥናት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትና የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የመስክ ምልከታ ይካዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም የተሻሻለው የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ መተዳደሪያ ደንብ እንደሚጸድቅና በከተሞች የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቋቋም በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት እንደሚደረግበትም ተመልክቷል።

Exit mobile version