አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከዘንድሮው የመኸር ሰብል 169 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ የተመራ ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ እና ጃማ ወረዳዎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
አቶ አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት÷በክልሉ የገጠመው የፀጥታ ችግር ሳይበግራቸው ውጤታማ ሥራ ላከናወኑ አርሶአደሮች እና ለአጠቃላይ የግብርና መዋቅር ምስጋና አቅርበዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ከዘንድሮው የመኸር ሰብል 169 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
በሰብል ጉብኝቱ ከፍተኛ የክልል እና የዞን አመራሮችም ተገኝተዋል።
በእሸቱ ወ/ሚካኤል