Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

19ኛው የከፍተኛ ንግድ ባለሙያዎች ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና 19ኛው የከፍተኛ የንግድ ባለሙያዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

ለሦስት ቀናት በሚቆየው ስብሰባም ስምምነቱን ወደ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችሉ ስምምነቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል፡፡

የከፍተኛ ንግድ ባለሙያዎቹ በኢንቨስትመንት፣ ዲጂታል ንግድ፣ የዕቃዎችና የአገልግሎት ንግድ ላይ አጀንዳዎችን አሰባስበው ለአባል ሀገራቱ የንግድ ሚኒስትሮች ስበሰባ ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

የአባል ሀገራቱ የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ ከአራት ቀናት በኋላ ጥቅምት 30 በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን÷ ሚኒስትሮቹም በአጀንዳዎቹ ላይ ተወያይተው ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉባዔን ከጥቅምት 11 ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች እያስተናገደች ነው፡፡

በመራኦል ከድር

Exit mobile version