Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰላምን ለማጽናት የመንግሥት ሠራተኛው የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላምን ለማጽናት የመንግሥት ሠራተኛው የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ጠየቁ፡፡

የባሕር ዳር ከተማና የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር የመንግሥት ሰራተኞች የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በዚህ ወቅት÷ወደ ዘላቂ ሰላም በመምጣት የልማት ስራ ላይ ትኩረት ለማድረግ ሰላምን ማጽናት የወቅቱ ዐቢይ አጀንዳ ነው ብለዋል።

የመንግሥት ትልቁ አቅም የመንግሥት ሠራተኛው ነው ያሉት ከንቲባው ሰላምን ለማጽናት የመንግሥት ሠራተኛው የበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።

ሰላም የሁሉም ሥራዎቻችን ቅድመ ሁኔታ መሆኑን በመገንዘብ መንግሥት ለዘላቂ ሰላም እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥረት መደገፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ሁሉም አካላት የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በደሳለኝ ቢራራ

Exit mobile version