የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲፈታ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

By amele Demisew

November 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች “ሁሉም ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እያደረጉ ነው።

ውይይቱ የክልሉን የጸጥታ ችግሮች ለመፍታት የተሰሩ የሰላም፣ የህዝብ ግንኙነት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ያመጡትን ዉጤቶች በማፅናት ዘላቂ ሰላም መገንባት የሚያስችል መተማመን ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የደሴ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ አለማየሁ በዚህ ወቅት÷ የወጣትና የአርሶ አደር ህይወት ቀጥፎ የሚመጣ የፖለቲካ ትርፍ የኪሳራ ቁልቁለት ነው ብለዋል፡፡

ሰላም ለማስፈን መነጋገር እንደሚገባ ገልጸው፤ በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲፈታ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የክልሉ ህዝብ ሰላምን ለማጽናት እርስ በርስ መመካከር እንዳለበት ጠቅሰው፤ ለዚህም በተደጋጋሚ የውይይት መድረክ እየተካሄደ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በእለኒ ተሰማ