Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ኢምፖርት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ በቻይና ዓለምአቀፍ ኢምፖርት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈች ነው።

ከኤክስፖው ጎን ለጎንም የሀገራት መሪዎች በዓለም ንግድና ኢንቨስትመንት እየመከሩ ነው።

ዛሬ በሻንጋይ በተከፈተውና 77 ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በሚሳተፉበት ኤክስፖ የኢትዮጵያ አስመጪና ላኪዎች ምርቶቻቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

ለሰባተኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ኤክስፖ ከመላው ዓለም የተወጣጡ 3 ሺህ 500 ኩባንያዎች እየተሳተፉ ሲሆን÷ ከእነዚህም መካከል 30 ያህሉ ከኢትዮጵያ የተውጣጡ ናቸው።

ኤክስፖው ከንግድና ኢንቨስትመንት ባለፈ የባህልና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር፣ የቢዝነስ ሽርክናን ለማጠናከርና የቱሪዝም ማስተዋወቂያ እድሎችን መፍጠርን ዓላማው አድርጎ የሚዘጋጅ ነው ተብሏል።

የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ የዓለምን ሰላም ለማረጋገጥ የጋራ ሰላምና ልማትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ቻይና ገበያዋን ለዓለም ክፍት ማድረጓንና ይህም በተለይም ለአዳጊ ሀገራት ተጨማሪ እድሎችን የሚሰጥ እንደሆነ ነው ያብራሩት።

በአፈወርቅ እያዩ

Exit mobile version