Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በውይይቶች ሕዝቡ ዘላቂ ሰላም የማስፈን ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል -አቶ ይርጋ ሲሳይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተካሄዱ ውይይቶች ሕዝቡ ዘላቂ ሰላም የማስፈን ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ ገለጹ፡፡

አቶ ይርጋ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ሕዝባዊ መድረኮች እና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች ያሉበትን የአፈፃፀም ደረጃ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በአማራ ክልል የተከሰተውን የጸጥታ ችግር በመቀልበስ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል ዘርፈ ብዙ የፀጥታና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

አመራሩ ከፀጥታ መዋቅሩና ሕዝቡ ጋር በቅንጅት በመስራቱ አበረታች ለውጥ እየመጣ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በተካሄዱ ውይይቶች ሕዝቡ ዘላቂ ሰላም የማስፈን ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል ያሉት ሃላፊው÷ በሁሉም አካባቢዎች የሕግ የበላይነት እስኪረጋገጥ ድረስ የሰላም ማስፈን ሥራው እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በቀጣይም ከመላ ሕዝቡ ጋር በቅንጅት በመስራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል ማለታቸውን የፓርቲው መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version