አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከቀድሞ የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያ ማንድራቶ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ በሚገኙ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡