አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ጎጃም ዞን ባሕርዳር ዙሪያ ወረዳ ሞሽ ቀበሌ በዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባው 120 ሜትር ተንጠልጣይ ድልድይ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።
የድልድዩ መገንባት በክረምት ወቅት በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ይደርስ የነበረን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ማስቀረት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
በአራት ቀበሌዎች የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በማስተሳሰር ልማትን እንደሚያፋጥን መጠቆሙንም የባሕርዳር ዙሪያ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።