የሀገር ውስጥ ዜና

በህንድ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ36 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Melaku Gedif

November 04, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ኡታራክሃንድ ግዛት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ቢያንስ 36 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ፡፡

በሰሜናዊ ኡታራክሃንድ ግዛት 44 ሰዎች አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ ወደ ገደል በመግባቱ በርካቶች ሲቆስሉ 36 ሰዎች መሞታቸውን የግዛቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ተሸከርካሪው ከቁጥጥር ውጪ በመሆን 50 ሜትር ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ መግባቱን ነው ባለስልጣናቱ የተናገሩት፡፡

የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በህንድ ዋነኛ የመጓጓዣ አማራጭ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ መሰል አደጋ በሀገሪቱ በተደጋጋሚ እንደሚከሰት ተነግሯል፡፡

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሶበች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሟች ቤተሰቦች 200 ሺህ፤ ጉዳት ለደረሰባቸው መንገደኞች ደግሞ 50 ሺህ ሩጲ ድጋፍ እንደሚደረግ መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በህንድ በየአመቱ 160 ሺህ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን፤ ይህም ሀገሪቱን የከፋ የትራፊክ አደጋ ከሚደርስባቸው ሀገራት መካከል እንድትጠቀስ ያደረጋት መሆኗን መረጃው ጠቁሟል።