Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ ቴሌኮም በአርባ ምንጭ ከተማ 5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን አስጀመረ።

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት ተቋማቸው ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ለዜጎች ዲጂታል መፍትሔ በመስጠት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጪን በመቀነስ ቀልጣፋ አገልግሎት ማቅረብ የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ማስፋፋት መርሐ-ግብር ዓላማ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክ ዲጂታል አገልግሎት ዕውን መሆን ከተሞችን በማዘመን፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል፡፡

አገልግሎቱ በአርባ ምንጭ መጀመሩ በሀገር ደረጃ ለተጀመረው ዲጂታል ሥርዓት አጋዥ  መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጋሞ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዓባይነህ አበራ ናቸው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የሚሰጣቸው ዘርፈ-ብዙ አገልግሎቶች መኖራቸውን ጠቁመው÷ አገልግሎቶቹን በይበልጥ በቀበሌዎች የማስፋፋት ተግባሩን እንዲጠናከር መጠየቃቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version