Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ማካሄድ ተጀምሯል።
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ የአስፈፃሚ ተቋማት ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በሩብ ዓመቱ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች የተከናወኑ የልማት የመልካም አስተዳደር ሥራዎች የዕቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ቀርቦ እየተገመገመ መሆኑንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡
Exit mobile version