የሀገር ውስጥ ዜና

ዜጎች ራሳቸውን ከኮቪድ 19 እየተከላከሉ  በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ለሀገር እንዲያስገኙ ጥሪ ቀረበ

By Tibebu Kebede

July 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁሉም ዜጋ ራሱን ከኮቪድ 19 እየተከላከለ በዘንድሮው በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ለሀገር አንዲያስገኙ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጥሪ አቀረቡ።

ጥሪውን ያቀረቡት የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፤ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ  እና የደንና የአየር ንብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ ናቸው።

የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹ በመልእክታቸውም፥ የጋራ ዘመቻው የጋራ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቱሩፋቶችን ያበረክታል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት የተተከለው አራት ቢሊየን ችግኞችም በአንድ አመት ውስጥ በርካታ የዲፕሎማሲ ድሎችን ማስገኘቱ ተጠቅሷል።

ከኮቪድ19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ሁሉም ክልሎች በራሳቸው መርሃ ግብር በተለየዩ ቀናት ተከልውን አንደሚያካሂዱ ሃላፊዎቹ ጠቅሰዋል።

ሁሉም ዜጎች ራሳቸውን በትክክለኛው መንገድ ከቫይረሱ እየተከላከሉ፤ አንደ ሀገር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች የሚያስገኘው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ግብ እውን እንዲሆን የበኩላቸወን አስተዋጽኦ አንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በትእግስት አብርሃም

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።