አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ53ኛው የኒው ዮርክ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ሳይቀናቸው ቀረ።
በወንዶች ታምራት ቶላና አዲሱ ጎበና የተወዳደሩ ሲሆን አትሌት ታምራት ቶላ 2:08:12 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል።
በተመሳሳይ በሴቶች ማራቶን አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ 2:27:14 በሆነ ሰዓት በመግባት 7ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።
አትሌት ጥሩነሽ ዲባባና ዴራ ዲዳ ውድድሩን አቋርጠው ወጥተዋል።
ውድድሩን በሴቶች ኬንያውያኑ ሼላ ቼፕኩሪ 2:24:35፣ ሄለን ኦብሪ 2:24:49 እና ቪቪያን ቺሪዮት 2:25:21 በሆነ ሰዓት ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
በወንዶች ደግሞ ከኔዘርላንድስ አትሌት አብዲ ነገይ 2:07:39 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ኬንያውያኑ ኢቫንስ ቺቤት 2:07:45 እንዲሁም አልበርት ኮሪር 2:08:00 በሆነ ሰዓት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።