አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት በመለያየት ነጥብ ተጋርተዋል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ተመጣጣኝ የሆነ እንቅስቃሴ ታይቷል።
የፕሪሚየር ሊጉ የ7ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርባምንጭ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡