Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ እንሰራለን – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልላችን ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ በትጋት እንሰራለን ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡

የአማራ ክልል ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ ሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ የሚመክር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት ርዕሰ መስተደድሩ÷ የክልላችን ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ የሚያስችል ስራ በትጋት እንሰራለን ብለዋል፡፡

ከተሞቻችን የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፍ ጎብኚዎች የሚመርጧቸው የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲሆኑ ለማስቻልም መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

በክልሉ በየደረጃው ያለው አመራር የክልሉን ከተሞች ዘመናዊ፣ ለነዋሪዎች ምቹና ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በቅንጅት እንዲሰሩና እንዲያስተባብሩ ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version