አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ማሌዢያ ኳላላምፑር ከተማን ጎብኝቷል፡፡፡
ልዑኩ በትናንትናው ዕለት ኳላላምፑር፣ ሳይበርጃን እና ሳንዌይ ከተሞችን የጎበኘ ሲሆን ፥ በዛሬው እለት ደግሞ የገንቲንግ የቱሪስት መዳረሻን በመጐብኘት ላይ ይገኛል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማ ፈጣን የልማት ለውጥ ያስመዘገበችዉ ማሌዢያ የተከተለችዉን የትራንስፎርሜሽን እስትራቴጂ በሚመለከት የልምድ ልውውጥ ለመውሰድ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡