Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ-ቴሌኮም ወላይታ ሶዶን ስማርት ከተማ ለማድረግ በቅንጅት እንደሚሠራ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ሶዶ ከተማን ስማርቲ ከተማ ለማድረግ የሚያስችሉ ቅደመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ የተጀመረውን ዲጂታል ሥርዓት በማዘመን በሁሉም ዘርፍ እምርታን ለማስመዝገብ በትብብር እየተሠራ ነው ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ፍሬው ሞገስ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ለሕብረተሰቡ የሚሰጥን አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ስማርት አገልግሎት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአገልግሎት አሰጣጥ ሒደት ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ ወደ ዲጂታል የመቀየር ሥራ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ለሚያደርገው ትብብር ምስጋና ማቅረባቸውንም የወላይታ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version