አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተሽከርካሪ የተለያዩ ክፍሎች በመደበቅ በኮንትሮባንድ ሊገቡ የነበሩ 83 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ከ4 ሺህ 100 በላይ ስማርት የሞባይል ስልኮች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው በተሽከርካሪ ጋቢና ጣራ ውስጥ ሻግ በማሰራት ጅግጅጋ ቦምባስ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሳይደርስ በጫካ በኩል አድርጎ ለማለፍ ሲሞከር በደረሰ መረጃ እና በተደረገ ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህም ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡