አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉን አስታወቀ።
በዚህም መሰረት፡-መገናኛ ውስጥ ተርሚናል ሲሰጡ የነበሩ ከመገናኛ – ቃሊቲ፣ ከመገናኛ – ሳሪስ፣ከመገናኛ – ጋርመንት መስመሮች÷በጊዜያዊነት መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው ከመገናኛ – ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ) መሆኑንም የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች ከመገናኛ – ገርጂ፣ከመገናኛ-ጎሮ፣ ከመገናኛ – አያት እና ከመገናኛ – ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ቢሮው አስታውቋል፡፡