Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን ለማስተናገድ የሚደረገውን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 38ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ለማስተናገድ እየተደረጉ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መገምገም የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

በመድረኩ ከ30 ተቋማት የተወጣጡ የብሄራዊ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በወቅቱ እንዳሉት÷ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን በአዲስ አበባ ማስተናገድ ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታ አለው።

ጉባኤው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ባለብዙ ወገን ትብብር ያጠናክራል ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ በዳዳ÷ ጉባኤውን በተሳካ መልኩ ማስተናገድ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን በተመለከተ ለአባላቱ ገለፃ አድርገዋል፡፡

38ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ ጉባኤ በፈረንጆቹ የካቲት 15 እና 16 ቀን 2025 ሲካሄድ፤ 46ኛው የህብረቱ የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ደግሞ የካቲት 12 እና 13 ቀን 2025 እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version