Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግስታት ስምምነት የተጀመረውን የላሊበላ ፕሮጀክት በተመለከተ ውይይት ተደረገ 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መንግስታት ስምምነት የተጀመረውን የላሊበላ ፕሮጀክት በተመለከተ ውይይት ተደረገ።

በውይይት መድረኩ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከአካባቢው የሀይማኖት አባቶች እና ከሕዝብ ተወካዮች ጋር መክረዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መንግስት ስምምነት የተጀመረው የዘላቂ ላሊበላ ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን መጠበቅ፣ መንከባከብና መጠገን እንደሚገባ መገለጹን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

ቅርሱን በመቀናጀት ከመጠበቅ፣ ከመንከባከብና ከመጠገን ባሻገር የቱሪዝም ፋሲሊቲዎችን ለማልማት እና ለማስተዋወቅ እየተደረገ ያለውን ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል አቅጣጫ ተቀምጧል።

Exit mobile version