አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ በንቃት ለመሳተፍ እና በመድረኩ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ተቋማት የሚኖራቸውን ሚና ማጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የብሪክስ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የቴክኒክ ኮሚቴ 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዩ የፖሊሲ አማካሪ አምባሳደር ምኒልክ ዓለሙ እንደተናገሩት፤ ጉባዔው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች አስጠብቋል።
ጉባዔው የኢትዮጵያን ጥቅምና ፍላጎቶች ያስጠበቀ፣ አባል ሀገራቱ ለዓለም አቀፍ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ እና የተመድ ጸጥታ ምክር ቤት መሻሻል እንዲሁም በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች በዓለም አቀፍ መድረኮች ሚናቸው እንዲጨምር የብሪክስ አባል ሀገራት ቁርጠኝነት የታየበት መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ በንቃት ለመሳተፍ እና በመድረኩ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ተቋማት የሚኖራቸውን ሚና ማጠናከር እንዳለባቸው በስብሰባው መነገሩን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡