Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ትምህርት ሚኒስቴር የሪሚዲያል ፕሮግራም ተቋርጧል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን አስገነዘበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተማሪዎች አቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተቋርጧል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ትምርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች አቅማቸውን በማሻሻል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲገቡና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እየተደረገ እንደሚገኝም አስታውሷል።

ይሁንና ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ትምህርት ሚኒስቴር የሪሚዲያል ፕሮግራም በበጀት ዕጥረት መቋረጡን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ገልጿል።

Exit mobile version