Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ጉልህ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና መርሃ-ግብር ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ጉልህ ሚና ለነበራቸው መንግስታዊና የግል ተቋማት የምስጋናና የዕውቅና መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር)÷ ጉባዔው እንዲሳካ በጋራ ተቋማት እና ግለሰቦች ተቀናጅተው ሰርተዋል።

በዚህም እንግዶች በቆይታቸው እንዲደሰቱና ለተደረገላቸው መስተንግዶ ሁሉ አመስግነው እንዲሄዱ መቻሉን ገልጸው፤ ለዚህም አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በጉባዔው ሁለት ነገሮችን ማሳካት ችለናል ያሉት ሚኒስትሯ፤ አንደኛው ያለን የተቀናጀ የጋራ አመራር መስጠት መቻል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እንደ ጸጥታ ዘርፍ እየሄድንበት ያለው ሪፎርም ስኬታማ መሆኑን መሳያ እንደሆነ ማሣየት ነው ብለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው÷ ጉባዔው ከጥቅምት 5 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መካሄዱን አስታውሰው፤ ጉባዔው በስኬት እንዲከናወን ጉልህ ድርሻ ለነበራቸው የመንግስትና የግል ተቋማት፣ የመከላከያ ክፍሎች እንዲሁም ልዩ ሚና ለነበራቸው ግለሰቦች ምስጋና ማቅረብ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

Exit mobile version