አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከ2 ሺህ በላይ መጻሕፍት እና “ኦርካም ማይ አይ” የተባለ ዐይነ ስውራን አንባቢያንን የሚያግዝ መሳሪያ ለአብርኾት ቤተ-መጻሕፍት አበረከቱ፡፡
ድጋፍ የተደረጉት መጻሕፍትም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለአንባቢያን በተለይም ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠቅላላ ዕውቀትን የሚሰጡ የመጻሕፍት ስብስብ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
መጻሕፍቱ ቡክ ፎር አፍሪካ ከተባለ ድርጅት በድጋፍ የተገኙ መሆናቸውን የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡