አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ 20 ሚሊየን ጫጩቶች መከፋፈላቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የሩብ ዓመቱን አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከነዚህም መካከል 20 ሚሊየን ጫጩቶች መከፋፈላቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በ2016/17 በጀት ዓመት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኞች ባለፉት 6 ዓመታት ደግሞ 40 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውንም ተናግረዋል፡፡
ወደ ውጭ ከተላኩ የግብርናው ዘርፍ ምርቶች 796 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ገልጸው፤ ከቡና ብቻ 519 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ነው የተናገሩት፡፡
በሌላ በኩል ዘንድሮ ከታቀደው አጠቃላይ 80 ቢሊየን የሴፍትኔት መርሐ ግብር 45 ቢሊየን ብር ለገጠር መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል፡፡
በታሪኩ ወ/ሰንበት እና በመሳፍንት እያዩ