አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ ሥራ የጀመረው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከትናንት ጀምሮ ምርትን ለገበያ መቅረቡን አስታወቀ፡፡
ፋብሪካው የማምረት ሥራውን በፍጥነት እንዲጀምር የተደረገው ምርቱን በቶሎ ወደ ገበያ በማቅረብ በሀገር ደረጃ ያለውን የሲሚንቶ ገበያ ለማረጋጋት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ምርቱ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ከግብዓት ምርት ጀምሮ ዘመናዊና የተደራጀ ላቦራቶሪ ገንብቶ ባለሙያ መድቦ በብቃት እየሠራ መሆኑን ነው ፋብሪካው ያስታወቀው፡፡
በዚህም ምርቱ ከሚመለከተው አካል የጥራት መስፈርት ያሟላ ነው መባሉን የፋብሪካው መረጃ አመላክቷል፡፡