Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮሪደር ልማቱ የኢትዮጵያን ስም ከፍ ያደርጋል- ጋዜጠኞች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመዲናዋ የኮሪደር ልማትና ውብ የቱሪዝም መዳረሻዎች የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉ መሆናቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች ገለጹ።

“ሚዲያ ለብሔራዊ ትርክትና ሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ ለመገናኛ ብዙኃን አመራሮችና ባለሙያዎች ለሦስት ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያም የብሔራዊ እዮቤልዩ ቤተ-መንግሥት እድሳትን ጨምሮ በአዲስ አበባ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በዚሁ ወቅት ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ጋዜጠኞች እንደገለጹት÷ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገን በማስተሳሰር የሚያሳዩ ናቸው፡፡

በመንግሥት ቃል የተገቡ ሥራዎች በተጨባጭ መሬት ላይ መውረዳቸውን ተመልክተናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ ለሀገር ዕድገት የድርሻውን እንዲወጣ በመንግሥት የተገነቡ ውብ የመስኅብ ስፍራዎችን መገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅ እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተዋል፡፡

አዲስ አበባን ለዓለም እና አኅጉራዊ ጉባዔዎች ተመራጭ የሚያደርጉ የቱሪዝም መዳረሻዎች መገንባታቸውንም ተመልክተናል ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version