አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከኮሜሳ አባል ሀገራት ጋር በቅርበት በመስራት ሰፊ ሀገራዊ ውህደትና ትብብር ለማድረግ ጥረት ታደርጋለች ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ አረጋገጡ፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በ23ኛው የኮሜሳ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም ለአዲሱ የኮሜሳ ሊቀመንበር ፕሬዚዳንት ኤቫርስቴ ንዳዪሺሚዬ ኮሜሳን ሲመሩ ላደረጉት የማይናወጥ ድጋፍ ስላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነዋል።
የአፍሪካን የእሴት ሰንሰለት ተግዳሮቶች መፍታት ጋር አያይዘው ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ በግብርና እና ቱሪዝም ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች እያሳየች መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዚህም አመርቂ ውጤቶች በመታየታቸው በምግብ ማለትም በስንዴ ራስን መቻል እና አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል።
አክለውም ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከኮሜሳ ሴክሬታሪያት እና ከሁሉም አባል ሀገራት ጋር በቅርበት በመስራት ጥልቅ እና ሰፊ አህጉራዊ ውህደት እና ትብብር በማድረግ ትቀጥላለች ሲሉም አረጋግጠዋል።