Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዲፕሎማሲን  በሚመለከት ለምክር ቤት አባላት ከሰጡት ማብራሪያ መካከል፡-

👉 የኢትጵያ ፖሊሲ ከተቻለ ከሁሉም ጋር በሰላምና በትብብር እንዲሁም ሰጥቶ በመቀበል መርህ መኖር ነው፤ ከሰላም ትርፋማ ስለምንሆን፡፡

👉 ስለብሔራዊ ጥቅማችን እንዴት እንተባበር በሚል ነው የምንሰራው፡፡ ከዚህ ቀደም ደሃ ናቸው፣ በውስጣቸው ችግር አለባቸው፣ ፍላጎታቸውን እንዳሻቸው አያደርጉም ብለው የሚያስቡ ከባቢዎች ካሉ አሁን መታረም አለባቸው፡፡

👉 ለምሳሌ ስንዴ አልለማም የሚለውን ሀሳብ ለማስተጋባት ስንዴ ከዩክሬን ወደ ኢትዮጵ መጣ የሚል ዜና ዓለም ሁሉ ይናገራል፤ እየነገሩን ያሉት ተረጋጉ ነው አንረጋጋም ፈጥነን እንለማለን፤ ያን ስብከት እማ ሰምተን ኖርን እኮ አሁን በቃን ድህነት አስጠላን፤ ለውጥ እንፈልጋለን፡፡

👉 ኢትዮጵያ ከራሷ ባለፈ ለአፍሪካ ልማት ቁርጠኛ ናት፡፡ ከየትኛውም ጎራ ጋር ሳንሰለፍ ከሁሉም ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ለብሔራዊ ጥቅማችን እንሰራለን፡፡

👉 ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን በመገንዘብ ሀገርን አስቀድሞ መስራት አለበት፡፡ በውስጥ የሚኖረን አንድነትና ሰላም ለዲፕሎማሲያዊ ጥንካሬያችን ከፍተኛ ሚና አለው፡፡

👉 ከዓረብ ሀገራት ጋር ያለንን ዝምድና በደምብ መመርመርና ጠንካራ ወዳጅነት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ ገንዘብ አላቸው እውቀት አላቸው፣ ልምድ አላቸው ለልጆቻችን የሥራ ቦታ ናቸው፡፡

👉 ከእስላሚክ የትብብር ድርጅት ተቋም ውስጥም ንግግር ጀምረናል፤ ስለማይፈልጉን ነው እንጂ ዓረብ ሊግም ብናገኝ እንገባለን፤ በገባንበት ቦታ ድምጻችንን እናሰማለን፤ ብሪክስ ሲባል አቅልላችሁ እናዳታዩት ጠቃሚ ነገር ነው፡፡

👉 ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ኢትዮጵያ የሶማሊያን ግዛት ልትወስድ ተስማማች የሚል እሳቤ ለመፍጠር ተሞክሯል፡፡ እኛ ግን ከሶማሌላንድ ጋር ስንፈራረም የ90 ዓመት ጠይቀን የ50 ዓመት ሊዝ ነው የተፈቀደልን፡፡ እንዴት ነው የ50 ዓመት ሊዝ መሬት መቀማት የሚሆነው፤ በርካቶች የ50 ዓመት አትፈርሙ 100 መሆን አለበት ጥሉንም ነበር፤ አልተሳካም እንጂ፡፡

👉 ኢትዮጵያ ራሷን ልታስፋፋ ነው የሚባለው ግን ስህተት ነው፤ እኛ ከሶማሊያ ጋር አጀንዳ የለንም እኛ አጀንዳችን የኢኮኖሚያችንና ሕዝባችን ዕድገት ነው፡፡

👉 ከኤርትራም ሆነ ከጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኬንያ ለኢትዮጵያ የሚያዋጣት ሰላማዊ ጉርብትና ነው፡፡

👉 ኢትዮጵያን አክብሮ የኢትዮጵያን ጉርብትና ወዶ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ጥቅም በደስታ ችግር የለውም፤ በምዝበራ ግን መሆን የለበትም፡፡ ከዚህ ውጭ ከምዕራቡም ከምስራቁም ተባብረን ነው ሀገር መገንባት የምንፈልገው፡፡

👉 እኛ ቅጥረኞች ሳንሆን ዓርበኞች ነን፣ ኢትዮጵያን መገንባት እንፈልጋለን፤ ይህንን አምኖ ያከበረ ማንም ሀገር በከፍተኛ ደስታ አብረን መስራት እንፈልጋለን፡፡

👉 ከኤርትራ ጋር አንዳንድ ወሬ ይነሳል፤ የምንፈልገው ሰላም ነው፤ ከዛ የከፋ ነገር ካልመጣ በስተቀር በእኛ ፍላጎት በኤርትራ ወንድሞቻችን ላይ ምንም ነገር አይፈጸምም፡፡

Exit mobile version