የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላምና ጸጥታን በሚመለከት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከሰጡት ማብራሪያ መካከል፡-

By ዮሐንስ ደርበው

October 31, 2024

👉 ከኃይል ይልቅ ሰላም በእጅጉ አዋጪ መንገድ ነው፡፡ ኃይል የግልፍተኝነት ስሜት ስላለበት ያልተገባ ጉዳት ያመጣል፡፡

👉 መሳሪያ ሲያዝ ብቻ አይደለም፤ ከመሳሪያ ውጭም ቤት ውስጥ ኃይል ስንቀላቅል ያለው ግንኙነትና ከኃይል ውጭ ያለው ፍጹም የተለያየ ነው፡፡

👉 ሰላምን አስታኮ ለተነሳው ጥያቄ ያለው መሻት ሰላም እንዲኖር ያለው ፍላጎት ተገቢና ትክክለኛ ነው፡፡

👉 ሁላችንም ለምናስበው ነገር ሰላም ወሳኝ መሆኑን መረዳት እና ለዚህም መረባረብ ይገባል፡፡

👉 ሰው የሚያመዛዝን ፍጡር ነው፤ አመዛዝኖ በዝቀተኛ ወጪ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኙ ነገሮችን ይመርጣል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለሚያገኘው ጥቅም የማይመጣጠን ከፍተኛ ወጪን አይመርጥም፡፡ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከመሞትና ከመግደል በሰላማዊ መንገድ መታገልን፤ ጊዜ ቢወስድም ውጤቱ የተሻለ ስለሆነ ሰው አመዛዝኖ ይመርጣል፡፡

👉 ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፡፡ ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን፤ አንፈልገውም፡፡

👉 ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ ነው፡፡ መንግስት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ቅድሚያ ሰጥቶ ሰርቷል፡፡

👉 አሁንም ያለን አቋም የትኛውም አይነት አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ ነው፡፡ ነገር ግን የትኛውም አካል በኃይል እና ጥላቻ መጠፋፋትን እንጂ ዓላማውን ማሳካት አይችልም፡፡ ሰከን ብሎ ማሳብ ይገባል፡፡ ሃሳብ አልባ ትግል ፍሬ የለውም፡፡

👉 በሰላም መኖር በአነስተኛ ኢንቨስትመንት የተሻለ ነገር ማምጣት ተመራጭ የሆነባቸው ሰዎች፣ ከባቢዎች፣ ስብስቦች ቢኖሩም አልፎ አልፎ ያን አማራጭ የማይመርጡ ሰዎች ደግሞ አሉ፡፡

👉 መኖሪያ ቤት መገንባት ብቻውን ሰላምን አያረጋግጥም፤ ሰላም፣ ልማትና ስራ መፍጠር በጣም አስፈላጊ እንደሆነው ሁሉ ማረሚያ ቤት መገንባትም ያስፈልጋል፡፡

👉 248 ሺህ የድሀ ቤት ገነባን ባልኳችሁ ቁጥር ልክ ማረሚያ ቤት አልገነባንም፤ ግን ቁጥሩ ቢያንስም መገንባት እንዳለብን መረዳት ይገባል፡፡