የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-

By ዮሐንስ ደርበው

October 31, 2024

👉 ባለፉት ሦስት ወራት 180 ቢሊየን ብር ገቢ ሰብስበናል፡፡ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 109 ቢሊየን ብር ነበር የተሰበሰበው፡፡ የልዩነቱ ስፋት ለውጥ እንዳለ እና መንገዳችን ትክክል እንደሆነ አመላክች ነው፡፡

👉 በፌደራል መንግሥት 900 ቢሊየን ብር በክልሎች ደግሞ 600 ቢሊየን ብር ገቢ መሠብሰብ ከተቻለ በአጠቃላይ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ገደማ እንሰበስባለን ማት ነው፡፡ ይህም በቂ ባይሆንም ትልቅ እመርታ ነው፡፡

👉 ሪዘርቭን በተመለከተ ደግሞ የብሔራዊ ባንክ ሪዘርቭ 161 በመቶ አድጓል፡፡

👉 የግል ባንኮች ሪዘርቭ 29 በመቶ አድጓል፡፡

👉 ሬሚታንስን በተመለከተም ባለፉት ሦስት ወራት 24 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

👉 ባንኮች 652 ሚሊየን ዶላር ገዝተው 1 ቢሊየን ገደማ ዶላር ሸጠዋል፡፡

👉 ባለፉት ሦስት ወራት ከኤክስፖርት ምርቶች 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ለማግኘት አቅደን፤ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል፡፡ ይህ ትልቅ ስኬት ነው፡፡

👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሪፎርሙ ተጠቃሚ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ነው፡፡ 900 ቢሊየን ብር የተራዘመ ቦንድ አግኝቷል፡፡ ይህም የፋይናንስ ሴክተሩን ለመደገፍ ይውላል፡፡

👉 አሁን ላይ ባንኮች 3 ነጥብ 5 ትሪሊየን ሐብት ላቸው፡፡

👉 መታረም ያለባቸው ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆነው፤ በአጠቃላይ ባንኮች ከፍተኛ ዕድገት አስመዝግበዋል፡፡ ይህም የሪፎርሙ ውጤት ነው፡፡

👉 የኢኮኖሚ ሥርዓታችን እጅግ የተዘጋ ነበር፤ ይህም በወጪ ንግድ፣ በተኪ ምርቶች፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመት ላይ ኢትዮጵያ መጠቀም ያለባትን ያህል እንዳትጠቀም አድርጓት ቆይቷል፡፡ ከዚህ አኳያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን መሰረት የሚጥል ነው፡፡

👉 ባላፉት ሦስት ወራት በተለያየ መንገድ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ 3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር መጥቷል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ተመዝግቦበታል፡፡

👉 ባለፈው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ሃብት 400 ሚሊየን ዶላር ነበር፡፡

👉 በአጠቃላይ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው 27 ቢሊየን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ይጠበቃል፡፡