የሀገር ውስጥ ዜና

ከዚህ ዓመት ጀምሮ የምናንሠራራበት ጊዜ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

By amele Demisew

October 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንደ ሀገር የምናንሠራራበት ጊዜ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

በሰጡት ምላሽ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-

👉 እንደ ሀገር በተለያዩ ተቋማት እና ዘርፎች ሪፎርም ሥንሠራ ቆይተናል፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንደ ሀገር የምናንሠራራበት ጊዜ ነው፡፡ በርካታ ውጤቶችም ይጠበቃሉ፡፡ ቀጣዩ የማጽናት ጊዜ ይሆናል፡፡

👉 አንዳንዶች ትፈርሳላችሁ ቢሉም፤ እንደማንፈርስ እንደ ሀገር በተግባር እያሳየን ነው፡፡ ይህ ጥንካሬ በይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

👉 ባለፈው ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግበናል፤ ይህም እጅግ አበረታች እና ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሁሉ አስደማሚ ሆኗል፡፡

👉 በያዝነው ዓመት ደግሞ 8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ በቅንጅት ርብርብ እያደረግን ነው፡፡

👉 የግብርናው ዘርፍ ብቻ በዚህ ዓመት 6 ነጥበ1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ብለን እንጠብቃለን፤ ለዚህም አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግን ነው፡፡

👉 30 ሚሊየን ሔክታር መሬት በማረስ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል፡፡

👉 በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በደን ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በጥምር ግብርና በሁሉም መስክ ከፍተኛ የሆነ እምርታ ተመዝግቧል፡፡

👉 ባለፈው ዓመት ከቡና ምርት ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል፤ ዘንድሮ ከብራዚልና ቬትናም በስተቀር ኢትየጵያን የሚበልጣት የለም፤ በተያዘው ዓመት ከቡና ምርት 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ይጠበቃል፡፡

👉 በዚህ ዓመት ክረምት እና በጋ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ሐየክታር መሬት በስንዴ ምርት ይሸፈናል፤ ከዚህም 300 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንጠብቃለን፡፡

👉 ሰሊጥ፣ ለውዝ ፣ አኩሪ አተር እና ሌሎችም ቀድሞ ከነበራቸው የምርት ሁኔታ በእጅጉ ጨምሯል፡፡