አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመንገደኞች አገልግሎት ዘርፍ ከአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ በመሆን ነው ሽልማቱን ያሸነፈው፡፡
የሽልማት ሥነ-ሥራዓቱም በአሜሪካ ካሊፎረኒያ መካሄዱን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡
አየር መንገዱ በምርጥ የአገልግሎት ቡድን አባላት፣ በምርጥ መዝናኛ፣ በምርጥ ምግብ እና መጠጥ፣ በምርጥ የመቀመጫ ወንበር እና በምርጥ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቦት ከአፍሪካ የላቀ አፈጻጸም ማሳየቱ ተገልጿል፡፡