አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ባሕር ዳር ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡
የባሕር ዳር ከተማን ግቦችም ፍሬው ሰለሞን እና ፍጹም ዓለሙ አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ 1 ሠዓት ላይ በተካሄደው የዛሬ መርሐ-ግብር ዎላይታ ድቻ ሀድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ካርሎስ ዳምጠው በ67ኛው ደቂቃ ኳሷን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡