Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጃፓን ለኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ ታምርት ቅናቄንና አቅም ያላቸው አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ የዘርፉን ምርታማነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
አቶ መላኩ÷ጃፓን የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን በጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ይካ) በኩል እያደረገች ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ዘርፉን በመደገፍ ውጤታማና ተወዳዳሪ ማድረግ የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት በቀላሉ ማሳለጥ የሚያስችል በመሆኑ ይካ ድጋፉን እዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡
ጃፓን ለአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት ዋና ማሳያ ሞዴል ሀገር መሆኗን ጠቅሰው÷ኢትዮጵያም ለአምራች ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት የተመቸ ፖሊሲና አሰራር ስርዓት እንዳላት አስረድተዋል፡፡
የጃፓን ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በዘርፉ እንዲሰማሩ እንዲያደርጉ አምባሳደሩን መጠየቃቸውንም የሚኒስቴርሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ በበኩላቸው÷በርካታ የጃፓን ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸው÷ ፍላጎቱ ወደ ተግባር እንዲቀየር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
Exit mobile version