Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብድር ጫና ያለባቸውን ሀገራት ዕዳ መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የብድር ጫና ያለባቸው የአፍሪካ ሀገራትን ዕዳ መቀነስ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክርር ተካሂዷል፡፡

የውይይት መድረኩን ያዘጋጁት አበዳሪ ተቋማት እና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም  ሲሆን÷ በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ የአፍሪካ ሀገራት ያለባቸውን የብድር ጫና መቀነስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ በተካሄደው ምክክር ተሳትፏል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልዑክ በኢትዮጵያ ዘላቂ እድገት እና ልማትን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በተደረገ የውይይት መድረክም ተሳትፏል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት እና ምሁራን ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱም በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ሥራዎች፣ ያሉ መልካም ድሎች፣ ስለሚኖሩ ተግዳሮቶች እንዲሁም መተግበር ስላለባቸው የመፍትሔ ሐሳቦች ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

Exit mobile version