Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ጋምቢያ ነባሩን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በማሻሻል ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጋምቢያ ነባሩን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነት በማሻሻል ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ እና በጋምቢያው አቻ ተቋም መካከል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ ጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በረራ ሲጀምር ያለምንም የምልልስ እና የመዳረሻ ቦታዎች ገደብ ወደ ጋምቢያ እና ከጋምቢያ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በረራ ማድረግ ያስችለዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ ከጋምቢያ ከአፍሪካ ውጭ ወደ ሌሎች ሀገሮች የሚደረጉ በረራዎች በጋምቢያ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፈቃድ ማካሄድ ያስችላል መባሉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version